ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ለሰዎች የማንበብ እንዲሁም የንግግርና የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል እንዲረዳህ ታስቦ ነው።
የበላይ አካሉ መልእክት
ለሰው ልጆች ከተሰጡት መልእክቶች ሁሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን መልእክት የማስተላለፍ መብት አለን።
ጥናት 4
ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ
አንድን ጥቅስ ከማንበብህ በፊት አድማጮችህ ለጥቅሱ ጉጉት እንዲያድርባቸው ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ አስብ።
ጥናት 6
የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ
አድማጮችህ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባሉት ቃላትና በምታብራራው ዋና ነጥብ መካከል ያለውን ዝምድና ማስተዋል እንዲችሉ እርዳቸው።
ጥናት 8
ትምህርት አዘል ምሳሌዎች
የአድማጮችህን ትኩረት የሚስቡና ዋናውን ነጥብ ለማጉላት የሚረዱ ቀለል ያሉ ምሳሌዎችን በመጠቀም ንግግርህ ማራኪ እንዲሆን ማድረግ ትችላለህ።
ጥናት 10
ድምፅን መለዋወጥ
የድምፅህን መጠን፣ ውፍረትና ቅጥነት እንዲሁም የምትናገርበትን ፍጥነት በመለዋወጥ የአድማጮችህን ስሜት ለመቀስቀስና እነሱን ለተግባር ለማነሳሳት ጥረት አድርግ።
ጥናት 13
የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
አድማጮችህ፣ ትምህርቱ ከሕይወታቸው ጋር እንዴት እንደሚያያዝ እንዲሁም የተማሩትን ነገር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያስተውሉ እርዳቸው።
ጥናት 14
ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ
አድማጮችህ ንግግርህን በትኩረት እንዲከታተሉ እርዳቸው፤ በተጨማሪም እያንዳንዱ ዋና ነጥብ ከንግግርህ ዓላማና ጭብጥ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ግልጽ አድርግላቸው።
ጥናት 16
አዎንታዊና የሚያበረታታ
ነቃፊ ከመሆን ይልቅ የሚያበረታታ ንግግር ለማቅረብ ጥረት አድርግ። አድማጮችህ በአምላክ ቃል ውስጥ በሚገኘው መንፈስን የሚያድስ እውነት ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ።
የምታደርገውን መሻሻል ገምግም
የማንበብና የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል በምትጥርበት ጊዜ የምታደርገውን መሻሻል ገምግም።
እነዚህንስ አይተሃቸዋል?
ተከታታይ ቪዲዮዎች
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ—ቪዲዮዎች
የማስተማር እንዲሁም ለሰዎች የማንበብ ችሎታህን ለማሻሻል የሚያስፈልጉህን ክህሎቶች ለማዳበር እነዚህን ቪዲዮዎች ተጠቀም።