ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
ከአምላክ የመጣው ምሥራች ምንድን ነው? በዚሀ ምሥራች ማመን የሚኖርብንስ ለምንድን ነው? ይህ ብሮሹር ለተለመዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
ከዚህ ብሮሹር ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?
ይህ ብሮሹር የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ጥቅም እንድታገኝ ይረዳሃል። ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ ጥቅስ ማውጣት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተማር።
ትምህርት 1
ምሥራቹ ምንድን ነው?
ከአምላክ የመጣው ምሥራች ምን እንደሆነ፣ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያትና ምን ማድረግ እንደሚኖርብን ለማወቅ ይህን ርዕስ ማንበብ ትችላለህ።
ትምህርት 4
ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
ኢየሱስ መሞት ያስፈለገው ለምንድን ነው? ቤዛ ምንድን ነው? ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ ምን እያደረገ ነው? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ጥረት አድርግ።
ትምህርት 5
አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ምድርን ለምን እንደፈጠረ፣ መከራ መቼ እንደሚወገድ፣ የምድርም ሆነ የሰዎች የወደፊት ዕጣ ምን እንደሆነ ያብራራል።
ትምህርት 8
አምላክ ክፋትና መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?
ክፋት የጀመረው እንዴት ነው? አምላክ መከራና ሥቃይ እስከ አሁን እንዲቀጥል የፈቀደው ለምንድን ነው? መከራና ስቃይ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?
ትምህርት 9
ቤተሰብህ ደስተኛ መሆን የሚችለው እንዴት ነው?
ደስተኛ አምላክ የሆነው ይሖዋ ቤተሰቦች ደስተኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ ለባሎች፣ ለሚስቶች፣ ለወላጆችና ለልጆች የሚሰጠውን ጠቃሚ ምክር ለማወቅ ይህን ጽሑፍ አንብብ።
ትምህርት 10
እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተህ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?
እውነተኛው ሃይማኖት አንድ ብቻ ነው? እውነተኛውን ሃይማኖት ለይቶ ለማወቅ ስለሚያስችሉት አምስት ምልክቶች ምርምር ማድረግ ትችላለህ።
ትምህርት 11
የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚጠቅሙን እንዴት ነው?
ኢየሱስ መመሪያ የሚያስፈልገን ለምን እንደሆነ ብሎም ዋነኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ እንደሆኑ ተናግሯል።
ትምህርት 12
ወደ አምላክ መቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?
አምላክ ማንኛውንም ዓይነት ጸሎት የሚሰማ መሆን አለመሆኑን፣ እንዴት መጸለይ እንዳለብንና ወደ አምላክ ለመቅረብ ምን ሌላ ነገር ማደረግ እንዳለብን መማር ትችላለህ።
ትምህርት 15
እውቀት መቅሰምህን መቀጠል ያለብህ ለምንድን ነው?
ስለ አምላክም ሆነ ስለ ቃሉ የምትቀስመው እውቀት ሌሎችን የሚጠቅመው እንዴት ነው? ከአምላክ ጋር ምን ዓይነት ዝምድና መመሥረት ትችላለህ?