ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ይህ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዳ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የያዘውን ሐሳብ እንድታውቅ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፤ ለምሳሌ ያህል መከራ የሚደርስብን ለምንድን ነው? ስንሞት ምን እንሆናለን? ደስተኛ የቤተሰብ ሕይወት ሊኖረን የሚችለው እንዴት ነው? እና ሌሎችም።
የአምላክ ዓላማ ይህ ነበር?
በዛሬው ጊዜ በሰዎች ላይ የሚደርሱት ችግሮች ይህን ያህል የበዙት ለምን እንደሆነ አስበህ ታውቃለህ? መጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ ስለሚመጣው አስደናቂ ለውጥ ይናገራል፤ አንተም ይህ በሚሆንበት ጊዜ ከሚኖረው በረከት ተቋዳሽ መሆን ትችላለህ።
ምዕራፍ 1
አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው?
አምላክ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልህ ይሰማሃል? ስለ አምላክ ባሕርያት እንዲሁም ወደ እሱ መቅረብ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተማር።
ምዕራፍ 2
መጽሐፍ ቅዱስ —አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠው መጽሐፍ
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያጋጥሙህን ችግሮች እንድትቋቋም ሊረዳህ የሚችለው እንዴት ነው? ትንቢቶቹን እምነት ልትጥልባቸው የምትችለው ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 4
ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
ኢየሱስ አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ ነው የምንለው ለምንድን ነው? የመጣው ከየት ነው? የይሖዋ አንድያ ልጅ ተብሎ የተጠራውስ ለምንድን ነው? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።
ምዕራፍ 7
በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ያላቸው እውነተኛ ተስፋ
በሞት ያጣሃቸው የምትወዳቸው ሰዎች አሉ? በሞት የተለዩህን ሰዎች እንደገና ልታገኛቸው ትችላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትንሣኤ ምን እንደሚያስተምር እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።
ምዕራፍ 8
የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
ብዙ ሰዎች ‘አባታችን ሆይ’ ወይም ‘አቡነ ዘበሰማያት’ ተብሎ የሚጠራውን ጸሎት ያውቁታል። ‘መንግሥትህ ትምጣ’ ብለን ስንጸልይ ምን ማለታችን ነው?
ምዕራፍ 9
የምንኖረው “በመጨረሻው ዘመን” ውስጥ ነው?
በዛሬው ጊዜ በዓለማችን ላይ የሚታዩት ክስተቶች እንዲሁም የሰዎች ባሕርይ የምንኖረው “በመጨረሻው ዘመን” ውስጥ መሆኑን ያረጋግጣሉ፤ እስቲ ማስረጃዎቹን ተመልከት።
ምዕራፍ 10
መንፈሳዊ ፍጡራን—ሊጠቅሙን ወይም ሊጎዱን የሚችሉት እንዴት ነው?
መላእክትና አጋንንት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሰዋል። እነዚህ መንፈሳዊ ፍጡራን በእርግጥ አሉ? በሕይወትህ ላይ ተጽዕኖ ሊየሳድሩ ይችላሉ?
ምዕራፍ 11
አምላክ በሰው ልጆች ላይ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው?
ብዙ ሰዎች በዓለም ላይ ለሚደርሰው መከራ ተጠያቂው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንተስ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለህ? በሰዎች ላይ መከራ ስለሚደርስበት ምክንያት አምላክ ምን እንደሚል ተመልከት።
ምዕራፍ 13
አምላክ ለሕይወት ያለው ዓይነት አመለካከት አለህ?
አምላክ ስለ ውርጃ፣ ደምን በደም ሥር ስለ መውሰድ እንዲሁም ስለ እንስሳት ሕይወት ምን ይሰማዋል?
ምዕራፍ 14
የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
ባሎች፣ ሚስቶች፣ ወላጆች እና ልጆች ኢየሱስ ካሳየው ፍቅር ብዙ ሊማሩ ይችላሉ። ኢየሱስ ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ምዕራፍ 16
ከእውነተኛው አምልኮ ጎን ቁም
ስለምታምንባቸው ነገሮች ለሌሎች ስትናገር ምን ተፈታታኝ ሁኔታ ሊያጋጥምህ ይችላል? ሌሎችን ሳታስቆጣ ስለ እምነትህ ልትነግራቸው የምትችለው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 17
በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
ስትጸልይ አምላክ ይሰማሃል? የዚህን ጥያቄ መልስ ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ምን እንደሚል ማወቅ ይኖርብሃል።
ምዕራፍ 18
ጥምቀትና ከአምላክ ጋር ያለህ ዝምድና
ብቃቱን ለማሟላት ምን እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል? መጠመቅ ምን ትርጉም አለው? ጥምቀት የሚከናወነው እንዴት ነው?
ምዕራፍ 19
ከአምላክ ፍቅር አትውጣ
አምላክ ላደረገልን ነገሮች ያለንን አድናቆት መግለጽ የምንችለው እንዴት ነው? ፍቅራችንን ማሳየት የምንችለውስ እንዴት ነው?
ተጨማሪ ክፍል
መለኮታዊው ስም—አስፈላጊነቱና ትርጉሙ
የአምላክ የግል ስም ከአብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ እንዲወጣ ተደርጓል፤ ለምን? በአምላክ ስም መጠቀም አስፈላጊ ነው?
ተጨማሪ ክፍል
የዳንኤል ትንቢት መሲሑ የሚመጣበትን ጊዜ አስቀድሞ የተናገረው እንዴት ነው?
አምላክ ከ500 ከሚበልጡ ዓመታት አስቀድሞ መሲሑ የሚመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ ተናግሯል። ስለዚህ አስደናቂ ትንቢት ተማር!
ተጨማሪ ክፍል
ኢየሱስ ክርስቶስ—አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ
ስለ መሲሑ የተነገሩት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በኢየሱስ ላይ ተፈጽመዋል። እነዚህ ትንቢቶች አንድም ሳይቀር እንደተፈጸሙ ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ በማየት አረጋግጥ።
ተጨማሪ ክፍል
አብን፣ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
ብዙ ሰዎች የሥላሴ መሠረተ ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚገኝ ያምናሉ። ይህ ትክክል ነው?
ተጨማሪ ክፍል
እውነተኛ ክርስቲያኖች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው?
ኢየሱስ የሞተው በመስቀል ላይ ነው? መልሱን በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመልከት።
ተጨማሪ ክፍል
የጌታ እራት—አምላክን የሚያስከብር በዓል
ክርስቲያኖች የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ እንዲያከብሩ ታዘዋል። ይህ በዓል መከበር ያለበት መቼና እንዴት ነው?
ተጨማሪ ክፍል
“ነፍስ” እና “መንፈስ”—የእነዚህ ቃላት ትርጉም ምንድን ነው?
ብዙ ሰዎች አንድ ሰው በሚሞትበት ጊዜ በዓይን የማትታይ ረቂቅ ነገር ከሰውየው ሥጋ ተለይታ መኖሯን ትቀጥላለች ብለው ያምናሉ። የአምላክ ቃልስ ምን ይላል?
ተጨማሪ ክፍል
ሲኦል ምንድን ነው?
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን ቃል “መቃብር” ወይም “ጉድጓድ” ብለው ተርጉመውታል። ይሁን እንጂ የዚህ ቃል ትክክለኛ ትርጉም ምንድን ነው?
ተጨማሪ ክፍል
1914—በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ዓመት
1914 ትልቅ ትርጉም ያለው ዓመት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ማስረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ?
ተጨማሪ ክፍል
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ማን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ኃያል መልአክ ማንነት ይነግረናል። ስለዚህ መልአክና በአሁኑ ጊዜ እያከናወነ ስላለው ነገር ተማር።
ተጨማሪ ክፍል
‘ታላቂቱ ባቢሎንን’ ለይቶ ማወቅ
የራእይ መጽሐፍ ‘ታላቂቱ ባቢሎን’ ስለምትባል ሴት ይናገራል። ቃል በቃል አንዲት ሴት ናት? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እሷ ምን ይናገራል?
ተጨማሪ ክፍል
ኢየሱስ የተወለደው በታኅሣሥ ወር ነው?
ኢየሱስ ተወለደ በሚባልበት ወቅት በቤተልሔም አካባቢ ምን ዓይነት የአየር ሁኔታ እንደነበረ ለማወቅ ሞክር። ይህ ምን ያስገነዝበናል?