መዝሙር 98:1-9
-
ይሖዋ፣ አዳኝና ጻድቅ ፈራጅ ነው
-
የይሖዋ ማዳን ታውቋል (2, 3)
-
ማህሌት።
98 ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+እሱ አስደናቂ ነገሮች አድርጓልና።+
ቀኝ እጁ፣ አዎ ቅዱስ ክንዱ መዳን አስገኝቷል።*+
2 ይሖዋ ማዳኑ እንዲታወቅ አድርጓል፤+በብሔራት ፊት ጽድቁን ገልጧል።+
3 ለእስራኤል ቤት ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የገባውን ቃል አስታውሷል።+
የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን* አይተዋል።+
4 ምድር ሁሉ፣ ለይሖዋ በድል አድራጊነት እልል በሉ።
ደስ ይበላችሁ፤ ደግሞም እልል በሉ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩ።+
5 ለይሖዋ በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤በበገናና ደስ በሚል ዜማ ዘምሩለት።
6 በእምቢልታና በቀንደ መለከት ድምፅ+በንጉሡ በይሖዋ ፊት በድል አድራጊነት እልል በሉ።
7 ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ፣መሬትና* በላይዋ የሚኖር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰሙ።
8 ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤ተራሮችም በአንድነት በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤+
9 እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና።*
በዓለም* ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በትክክል ይፈርዳል።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ድል አቀዳጅቶታል።”
^ ወይም “የአምላካችንን ድል።”
^ ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድርና።”
^ ወይም “መጥቷልና።”
^ ወይም “ፍሬያማ በሆነችው ምድር።”