ምሳሌ 6:1-35
6 ልጄ ሆይ፣ ለባልንጀራህ ዋስ* ብትሆን፣+የማታውቀውን ሰው እጅ ብትመታ፣*+
2 በገባኸው ቃል ብትጠመድ፣ከአፍህ በወጣው ቃል ብትያዝ፣+
3 ልጄ ሆይ፣ በባልንጀራህ እጅ ወድቀሃልና፣ይህን በማድረግ ራስህን ነፃ አውጣ፦
ሂድና ባልንጀራህን በትሕትና አጥብቀህ ለምነው።+
4 ይህን ሳታደርግ አትተኛ፤በዓይንህም እንቅልፍ አይዙር።
5 እንደ ሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣እንደ ወፍም ከወፍ አዳኝ እጅ ራስህን አድን።
6 አንተ ሰነፍ፣ ወደ ጉንዳን ሂድ፤+መንገዷንም በጥሞና ተመልክተህ ጥበበኛ ሁን።
7 አዛዥ፣ አለቃ ወይም ገዢ ባይኖራትም እንኳ፣
8 ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች፤+ቀለቧንም በመከር ወቅት ትሰበስባለች።
9 አንተ ሰነፍ፣ የምትጋደመው እስከ መቼ ነው?
ከእንቅልፍህ የምትነሳውስ መቼ ነው?
10 ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣+
11 ድህነት እንደ ወንበዴ፣እጦትም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።+
12 የማይረባና ክፉ ሰው ንግግሩ ጠማማ ነው፤+
13 በዓይኑ ይጣቀሳል፤+ በእግሩ ምልክት ይሰጣል፤ በጣቶቹም ይጠቁማል።
14 ጠማማ በሆነው ልቡ፣ነጋ ጠባ ሴራ ይጠነስሳል፤+ ጠብም ይዘራል።+
15 በመሆኑም ጥፋት በድንገት ይመጣበታል፤እንደማይጠገን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል።+
16 ይሖዋ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤እንዲያውም እሱ የሚጸየፋቸው* ነገሮች ሰባት ናቸው፦
17 ትዕቢተኛ ዓይን፣+ ውሸታም ምላስ፣+ ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣+
18 ክፉ ሐሳብ የሚያውጠነጥን ልብና+ ወደ ክፋት በፍጥነት የሚሮጡ እግሮች፣
19 ባወራ ቁጥር ውሸት የሚናገር ሐሰተኛ ምሥክርና+በወንድማማቾች መካከል ጠብ የሚዘራ ሰው።+
20 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፤የእናትህንም መመሪያ* ቸል አትበል።+
21 ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤በአንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።
22 በምትሄድበት ሁሉ ይመራሃል፤ስትተኛም ይጠብቅሃል፤ስትነቃም ያነጋግርሃል።*
23 ትእዛዙ መብራት ነውና፤+ሕጉም ብርሃን ነው፤+የተግሣጽ ወቀሳም ወደ ሕይወት ይመራል።+
24 ከክፉ ሴት፣+ ከባለጌ* ሴትምየሚያባብል አንደበት ይጠብቁሃል።+
25 ውበቷን በልብህ አትመኝ፤+የሚያማምሩ ዓይኖቿም አይማርኩህ፤
26 አንድ ሰው በዝሙት አዳሪ የተነሳ ለድህነት ይዳረጋልና፤*+አመንዝራ ሴት ደግሞ የሰውን ውድ ሕይወት* ታጠምዳለች።
27 በጉያው እሳት ታቅፎ ልብሱ የማይቃጠልበት ሰው አለ?+
28 ወይስ በፍም ላይ ተራምዶ እግሮቹ የማይቃጠሉበት ሰው ይኖራል?
29 ከባልንጀራው ሚስት ጋር የሚተኛ ሰውም እንደዚሁ ነው፤የሚነካት ሁሉ መቀጣቱ አይቀርም።+
30 ሌባ በተራበ ጊዜ ራሱን* ሊያጠግብ ቢሰርቅ፣ሰዎች በንቀት አያዩትም።
31 በተያዘ ጊዜ ግን ሰባት እጥፍ ይከፍላል፤በቤቱ ያለውን ውድ ነገር ሁሉ ያስረክባል።+
32 ከሴት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሁሉ ማስተዋል* ይጎድለዋል፤እንዲህ የሚያደርግ ሰው በራሱ* ላይ ጥፋት ያመጣል።+
33 የሚያተርፈው ነገር ቢኖር ቁስልና ውርደት ነው፤+ኀፍረቱም መቼም አይወገድም።+
34 ቅናት ባልን እጅግ ያስቆጣዋልና፤ለበቀል በሚነሳበት ጊዜም ፈጽሞ ርኅራኄ አያሳይም።+
35 ማንኛውንም ዓይነት ካሳ* አይቀበልም፤ምንም ያህል ስጦታ ብታቀርብለት ቁጣው አይበርድም።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ብትጨብጥ።” ቃል መግባትን ያመለክታል።
^ ቃል በቃል “ተያዥ።”
^ ወይም “ነፍሱ የምትጸየፋቸው።”
^ ወይም “ሕግ፤ ትምህርት።”
^ ወይም “ያስተምርሃል።”
^ ወይም “ነፍስ።”
^ ቃል በቃል “አንድ ሰው ያለውን ሁሉ አጥቶ አንድ ዳቦ ብቻ ይቀረዋል።”
^ ወይም “ነፍሱን።”
^ ቃል በቃል “ልብ።”
^ ወይም “በነፍሱ።”
^ ወይም “ቤዛ።”