ኢሳይያስ 56:1-12

  • የባዕድ አገር ሰውና ጃንደረባ የሚያገኙት በረከት (1-8)

    • ለሰው ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት (7)

  • ዕውር ጠባቂዎች፤ መናገር የማይችሉ ውሾች (9-12)

56  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ፍትሕን ጠብቁ፤+ ጽድቅ የሆነውንም አድርጉ፤ማዳኔ በቅርቡ ይመጣልና፤ጽድቄም ይገለጣል።+  2  ይህን የሚያደርግ ሰው፣ደግሞም ይህን አጥብቆ የሚይዝ፣ሰንበትን የሚጠብቅና የማያረክስ፣+እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ክፋት እጁን የሚመልስ የሰው ልጅ ደስተኛ ነው።  3  ከይሖዋ ጋር የሚቆራኝ የባዕድ አገር ሰው+‘ይሖዋ ከሕዝቡ እንደሚለየኝ ጥርጥር የለውም’ አይበል። ጃንደረባም ‘እነሆ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ’ አይበል።” 4  ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ሰንበቶቼን ለሚጠብቁ፣ ደስ የሚያሰኘኝን ነገር ለሚመርጡና ቃል ኪዳኔን አጥብቀው ለሚይዙ ጃንደረቦች፣  5  በቤቴና በቅጥሮቼ ውስጥከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚሻል ነገር፣ ይኸውም የመታሰቢያ ሐውልትና ስም እሰጣቸዋለሁ።ለዘላለም የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።  6  እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣  7  ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+ 8  የተበተኑትን የእስራኤል ሰዎች የሚሰበስበው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “አስቀድሞ ከተሰበሰቡት በተጨማሪ ሌሎችን ወደ እሱ እሰበስባለሁ።”+  9  እናንተ በሜዳ ያላችሁ አራዊት ሁሉ፣እናንተ በጫካ የምትኖሩ አራዊት ሁሉ፣ ኑና ብሉ።+ 10  ጠባቂዎቹ ዕውሮች ናቸው፤+ አንዳቸውም አላስተዋሉም።+ ሁሉም መናገር የማይችሉ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም።+ ተጋድመው ያለከልካሉ፤ እንቅልፍም ይወዳሉ። 11  በቀላሉ የማይጠግቡ* ውሾች ናቸው፤ጠገብኩ ማለትን አያውቁም። ማስተዋል የሌላቸው እረኞች ናቸው።+ ሁሉም በገዛ ራሳቸው መንገድ ሄደዋል፤እያንዳንዳቸው አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሻሉ፤ እንዲህም ይላሉ፦ 12  “ኑ! የወይን ጠጅ ላምጣናእስኪወጣልን ድረስ እንጠጣ።+ ነገም እንደ ዛሬ ይሆናል፤ እንዲያውም በጣም የተሻለ ይሆናል።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ብርቱ ነፍስ ያላቸው።”