ኢዮብ 36:1-33
36 ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2 “አምላክን ወክዬ ገና የምናገረው ነገር ስላለጉዳዩን በማብራራበት ጊዜ ትንሽ ታገሠኝ።
3 ስለማውቀው ነገር በሰፊው እናገራለሁ፤ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነም አስታውቃለሁ።+
4 በእርግጥ የምናገረው ቃል ውሸት አይደለም፤እውቀቱ ፍጹም የሆነው አምላክ+ በፊትህ ነው።
5 በእርግጥ አምላክ ኃያል ነው፤+ ደግሞም ማንንም ገሸሽ አያደርግም፤የማስተዋል ችሎታው* ታላቅ ነው።
6 የክፉዎችን ሕይወት አይጠብቅም፤+ጎስቋላው ግን ፍትሕ እንዲያገኝ ያደርጋል።+
7 ዓይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሳም፤+ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤*+ እነሱም ለዘላለም ከፍ ከፍ ይላሉ።
8 ይሁንና ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
9 ከመታበያቸው የተነሳ ስለፈጸሙት ድርጊትይኸውም ስለ በደላቸው ይነግራቸዋል።
10 እርማት እንዲቀበሉ ጆሯቸውን ይከፍታል፤ከክፋትም እንዲመለሱ ይነግራቸዋል።+
11 ቢታዘዙትና ቢያገለግሉት፣የሕይወት ዘመናቸውን በብልጽግና ይፈጽማሉ፤ሕይወታቸውም አስደሳች ይሆናል።+
12 ባይታዘዙ ግን በሰይፍ* ይጠፋሉ፤+ያለእውቀትም ይሞታሉ።
13 በልባቸው አምላክ የለሽ* የሆኑ ቂም ይይዛሉ።
እሱ በሚያስራቸው ጊዜም እንኳ እርዳታ ለማግኘት አይጮኹም።
14 ገና ወጣት እያሉ ይሞታሉ፤*+በቤተ መቅደስ ቀላጮች* መካከል ሕይወታቸውን ያሳልፋሉ።*+
15 ሆኖም አምላክ* የተጎሳቆሉ ሰዎችን ከጉስቁልናቸው ይታደጋቸዋል፤ጭቆና በሚደርስባቸው ጊዜ ጆሯቸውን ይከፍታል።
16 እሱ ከመከራ መንጋጋ አስጥሎ+የሚያጨናንቅ ነገር ወደሌለበት ሰፊ ስፍራ ያመጣሃል፤+ማዕድህ ምርጥ በሆነ ምግብ የተሞላ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ያጽናናሃል።+
17 ፍርድ ሲበየንና ፍትሕ ሲሰፍን፣በክፉዎች ላይ በሚፈጸመው ፍርድ ትረካለህ።+
18 ይሁንና ቁጣ ወደ ክፋት* እንዳይመራህ ተጠንቀቅ፤+ጠቀም ያለ ጉቦም አያስትህ።
19 እርዳታ ለማግኘት መጮኽህ፣ወይም የምታደርገው ማንኛውም ብርቱ ጥረት ከጭንቀት ነፃ ያደርግሃል?+
20 ሰዎች ካሉበት ስፍራ የሚጠፉበትንየሌሊቱን ጊዜ አትናፍቅ።
21 ከጉስቁልና ይልቅ ይህን መርጠህ፣+ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
22 እነሆ፣ አምላክ በኃይሉ ከፍ ከፍ ብሏል፤እንደ እሱ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
23 እሱን መንገድ የመራው፣*ወይም ‘የሠራኸው ነገር ትክክል አይደለም’ ያለው ማን ነው?+
24 ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣+የእሱን ሥራ ከፍ ከፍ ማድረግ አትዘንጋ።+
25 የሰው ልጆች ሁሉ አይተውታል፤ሟች የሆነ ሰው ከሩቅ ያያል።
26 አዎ፣ አምላክ እኛ ልናውቀው ከምንችለው በላይ ታላቅ ነው፤+የዘመኑም ቁጥር ከመረዳት ችሎታ በላይ ነው።*+
27 እሱ የውኃ ጠብታዎችን ወደ ላይ ይስባል፤+ጭጋጉም ወደ ዝናብነት ይለወጣል፤
28 ከዚያም ደመናት ያዘንባሉ፤+በሰው ልጆችም ላይ ዶፍ ያወርዳሉ።
29 የደመናትን ንብርብር፣ከድንኳኑም የሚሰማውን ነጎድጓድ+ ማን ሊያስተውል ይችላል?
30 መብረቁን*+ በላዩ ላይ እንዴት እንደሚዘረጋ፣የባሕሩንም ወለል* እንዴት እንደሚሸፍን ተመልከት።
31 በእነዚህም ሕዝቦችን ያኖራል፤*ምግብ አትረፍርፎ ይሰጣቸዋል።+
32 በእጆቹ መብረቁን ይሸፍናል፤ወደ ዒላማውም ይሰደዋል።+
33 ነጎድጓዱ ስለ እሱ ይናገራል፤ከብቶች እንኳ ሳይቀሩ ማን* እየመጣ እንዳለ ይጠቁማሉ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “የልቡ ኃይል።”
^ “ነገሥታትን በዙፋን ላይ ያስቀምጣል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “በመሣሪያ (በተወንጫፊ መሣሪያ)።”
^ ወይም “ከሃዲ።”
^ ወይም “ነፍሳቸው ትሞታለች።”
^ ግብረ ሰዶማውያን ሆነው የሴት ዓይነት ሚና ያላቸውን ወንዶች ያመለክታል።
^ “ሕይወታቸው ይቀጫል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ቃል በቃል “እሱ።”
^ ወይም “ይሁንና ቁጣ በንቀት ወደማጨብጨብ።”
^ “እሱን የተቸው፤ ተጠያቂ ያደረገው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “አይመረመርም።”
^ ቃል በቃል “ብርሃኑን።”
^ ቃል በቃል “ሥር።”
^ “ለሕዝቦች ይሟገታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ “ምን” ማለትም ሊሆን ይችላል።