ኤርምያስ 17:1-27

  • የይሁዳ ኃጢአት በጽላት ላይ ተቀርጿል (1-4)

  • በይሖዋ መታመን የሚያስገኘው በረከት (5-8)

  • ልብ ከዳተኛ ነው (9-11)

  • የእስራኤል ተስፋ የሆነው ይሖዋ (12, 13)

  • ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (14-18)

  • “የሰንበትን ቀን ቀድሱ” (19-27)

17  “የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብዕር ተጽፏል። በሾለ የአልማዝ ጫፍ በልባቸው ጽላትናበመሠዊያዎቻቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጿል፤  2  ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻቸው ከፍ ባሉ ኮረብቶች ላይ ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ አጠገብ ያሉትን+መሠዊያዎቻቸውንና የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ያስታውሳሉ፤+  3  በአውላላ ሜዳ ላይ ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትንም ያስባሉ። ንብረትህን ይኸውም ውድ ሀብትህን ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ፤+አዎ፣ በመላው ክልልህ ካለው ኃጢአት የተነሳ ከፍ ያሉ ቦታዎችህ እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ።+  4  የሰጠሁህን ርስት በገዛ ፈቃድህ አሳልፈህ ትሰጣለህ።+ በማታውቀውም ምድር ጠላቶችህን እንድታገለግል አደርግሃለሁ፤+ቁጣዬን እንደ እሳት አቀጣጥለሃልና።*+ እሳቱም ለዘላለም ይነዳል።”  5  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሰዎች የሚታመን፣+በሰብዓዊ ኃይል የሚመካና*+ልቡ ከይሖዋ የራቀ ሰው* የተረገመ ነው።  6  በበረሃ ብቻውን እንዳለ ዛፍ ይሆናል። መልካም ነገር ሲመጣ አያይም፤ይልቁንም በምድረ በዳ ደረቅ በሆኑ ስፍራዎች፣ማንም መኖር በማይችልበት የጨው ምድር ይኖራል።  7  በይሖዋ የሚታመን፣መመኪያውም ይሖዋ የሆነ ሰው* የተባረከ ነው።+  8  በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ሥሮቹን ወደ ጅረት እንደሚሰድ ዛፍ ይሆናል። ሙቀት ሲመጣ አያስተውልም፤ከዚህ ይልቅ ቅጠሉ ሁልጊዜ ይለመልማል።+ ድርቅ በሚከሰትበት ዓመትም ምንም አይጨነቅም፤ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።  9  ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ* ነው፤ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለስም።*+ ማንስ ሊያውቀው ይችላል? 10  እኔ ይሖዋ፣ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ፣እንደ ሥራውም ፍሬ ለመስጠትልብን እመረምራለሁ፤+የውስጥ ሐሳብንም* እፈትናለሁ።+ 11  በማጭበርበር* ሀብት የሚያከማች ሰው፣ያልጣለችውን እንቁላል እንደምትሰበስብ ቆቅ ነው።+ በዕድሜው አጋማሽ ላይ ሀብቱ ትቶት ይሄዳል፤በመጨረሻም የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው መሆኑ ይረጋገጣል።” 12  ከመጀመሪያ አንስቶ ክብራማ የሆነ ዙፋን ከፍ ከፍ ብሏል፤እሱም መቅደሳችን ነው።+ 13  የእስራኤል ተስፋ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ። አንተን* የሚክዱ ስማቸው በአፈር ላይ ይጻፋል፤+ምክንያቱም የሕያው ውኃ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ትተዋል።+ 14  ይሖዋ ሆይ፣ ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ። አድነኝ፤ እኔም እድናለሁ፤+የማወድሰው አንተን ነውና። 15  እነሆ፣ “የይሖዋ ቃል የት አለ?+ እስቲ ይፈጸም!” የሚሉኝ ሰዎች አሉ። 16  እኔ ግን እረኛ ሆኜ አንተን ከመከተል ወደኋላ አላልኩም፤የጥፋትንም ቀን ፈጽሞ አልተመኘሁም። አንተ ከንፈሮቼ የተናገሩትን ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤ሁሉም የተፈጸመው በፊትህ ነው! 17  ሽብር ላይ አትጣለኝ። አንተ በጥፋት ቀን መጠጊያዬ ነህ። 18  አሳዳጆቼ ኀፍረት ይከናነቡ፤+እኔ ግን ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ። እነሱ በሽብር ይዋጡ፤እኔ ግን አልሸበር። የጥፋት ቀን አምጣባቸው፤+አድቅቃቸው፤ ሙሉ በሙሉም አጥፋቸው።* 19  ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም።+ 20  እንዲህም በላቸው፦ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ፣ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሙሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። 21  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለራሳችሁ* ተጠንቀቁ፤ በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም አትሸከሙ ወይም በኢየሩሳሌም በሮች አታስገቡ።+ 22  በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም ከቤታችሁ ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ።+ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሁሉ እናንተም የሰንበትን ቀን ቀድሱ።+ 23  ሆኖም እነሱ አልሰሙም፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም፤ ላለመታዘዝና ተግሣጽ ላለመቀበል በእንቢተኝነታቸው ጸኑ።”’*+ 24  “‘“ይሁን እንጂ በሚገባ ብትታዘዙኝ” ይላል ይሖዋ፣ “በሰንበትም ቀን በከተማዋ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡና በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሥራ ባለመሥራት ቀኑን ብትቀድሱት፣+ 25  በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንት+ ይኸውም እነሱና መኳንንታቸው እንዲሁም የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤+ ይህችም ከተማ ለዘለቄታው የሰው መኖሪያ ትሆናለች። 26  ሰዎችም ከይሁዳ ከተሞች፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ ቦታዎች፣ ከቢንያም አገር፣+ ከቆላው፣+ ከተራራማው አካባቢና ከኔጌብ* ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎች፣+ መሥዋዕቶች፣+ የእህል መባዎች፣+ ነጭ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕቶች ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት ይመጣሉ።+ 27  “‘“የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በሮቿን በእሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም የኢየሩሳሌምን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤+ ፈጽሞም አይጠፋም።”’”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“በቁጣዬ እንደ እሳት ነደሃልና” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ሥጋን ክንዱ የሚያደርግና።”
ወይም “ብርቱ ሰው።”
ወይም “ብርቱ ሰው።”
ወይም “አታላይ።”
“ፈውስ የለውም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ጥልቅ ስሜትንም።” ቃል በቃል “ኩላሊትንም።”
ወይም “ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ።”
ቃል በቃል “እኔን።” ይሖዋን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “እጥፍ ድርብ ጥፋት አምጣባቸው።”
ወይም “ለነፍሳችሁ።”
ቃል በቃል “አንገታቸውን አደነደኑ።”
ወይም “ከደቡብ።”