መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 3 2021 | የወደፊት ሕይወትህን አስተማማኝ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
የወደፊት ሕይወትህን አስተማማኝ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? በዚህ መጽሔት ላይ ያሉት ተከታታይ ርዕሶች ሰዎች የሚሞክሯቸውን የተለያዩ አማራጮች ለመገምገም ይረዱሃል። በተጨማሪም የወደፊቱን ሕይወትህን በተመለከተ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምትችልበትን ብቸኛውን አማራጭ ይጠቁሙሃል።
አስተማማኝ የወደፊት ሕይወት—የሁሉም ሰው ምኞት
ድንገተኛና ያልተጠበቁ ክስተቶች የማኅበረሰቡን ኑሮ በሚያመሰቃቅሉበት ወቅት አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?
የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በምን ላይ ነው?
በኮከብ ቆጠራ፣ ጠንቋይ በመጠየቅ፣ በቀድሞ አባቶች አምልኮና በሪኢንካርኔሽን የሚያምኑ ብዙ ሰዎች በዓይን የማይታዩ ኃይሎች የወደፊት ሕይወታቸውን እንደሚቆጣጠሩት ይሰማቸዋል።
ትምህርትና ገንዘብ ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳሉ?
ብዙዎች ከፍተኛ ትምህርት መከታተልና ሀብት ማካበት ያልተጠበቁ ውጤቶችን እንደሚያስከትሉ አስተውለዋል።
ጥሩ ሰው መሆን ብቻ የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ያደርጋል?
ጥሩ ሰው መሆን አስፈላጊ ነው፤ ሆኖም ይህ ብቻውን የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ አያደርግም።
ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት ይቻላል?
ውሳኔ ስናደርግ በዕድሜም ሆነ በተሞክሮ ከእኛ የሚበልጥን ሰው እናማክራለን። ከወደፊቱ ጊዜ ጋር በተያያዘም አስተማማኝ መመሪያ ሊሰጠን የሚችል አካል አለ።
የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በአንተ ምርጫ ላይ ነው
የትኞቹ ምርጫዎች ቀርበውልናል?
የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ይመስልሃል?