መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሐምሌ 2018
ይህ እትም ከመስከረም 3 እስከ 30, 2018 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።
ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል
ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል—ምያንማር
በርካታ የይሖዋ ምሥክሮች የትውልድ አገራቸውን ትተው በመሄድ በምያንማር ያለውን የመከር ሥራ ለመደገፍ የተነሳሱት ለምንድን ነው?
እውቅና ማግኘት የምትፈልጉት በማን ዘንድ ነው?
አምላክ ለታማኝ አገልጋዮቹ እውቅና ከሚሰጥበት መንገድ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ዓይኖቻችሁ የሚመለከቱት ወዴት ነው?
ሙሴ ከሠራው ከባድ ስህተት ጠቃሚ ትምህርት ማግኘት እንችላለን።
“ከይሖዋ ጎን የሚቆም ማን ነው?”
ስለ ቃየን፣ ሰለሞን፣ ሙሴና አሮን የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ከይሖዋ ጎን መቆም የጥበብ እርምጃ የሆነው ለምን እንደሆነ ያስገነዝቡናል።
የይሖዋ ንብረት ነን
ይሖዋ ከእሱ ጋር ዝምድና የመመሥረት ውድ መብት ስለሰጠን አመስጋኝነታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
“ለሁሉም ዓይነት ሰዎች” ርኅራኄ አሳዩ
ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ነገርና ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ማስተዋላችንና እነሱን መርዳታችን ርኅራኄ በማሳየት ረገድ ይሖዋን ለመምሰል ያስችለናል።
መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይበልጥ ውጤታማና አስደሳች እንዲሆንልህ ማድረግ
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ይክስሃል።
የአንባቢያን ጥያቄዎች
አንድ ያልተጋቡ ወንድና ሴት አጠያያቂ በሆነ ሁኔታ አብረው ቢያድሩ ከባድ ኃጢአት እንደፈጸሙ ሊቆጠር ይችላል?