በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአይሁድ የቤተ መቅደስ ፖሊሶች እነማን ነበሩ? ሥራቸውስ ምን ነበር?

ካህናት ያልሆኑ ሌዋውያን ከሚያከናውኗቸው በርካታ ሥራዎች መካከል አንዱ ከፖሊስ ሥራ ጋር ይመሳሰል ነበር። ይህን ሥራ የሚያከናውኑት በቤተ መቅደሱ ሹም አመራር ሥር ሆነው ነው። የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ የሆነው ፋይሎ የእነዚህን ጠባቂዎች ሥራ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “ከእነዚህ [ሌዋውያን] መካከል አንዳንዶቹ በመግቢያው ላይ ዘብ ሆነው ይቆሙ ነበር፤ አንዳንዶቹ ደግሞ [በቤተ መቅደሱ] ውስጥ ከመቅደሱ ፊት ለፊት በመቆም ያልተፈቀደለት ሰው፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደዚያ እንዳይገባ ይከላከሉ ነበር። ሌሎቹ ደግሞ በፈረቃ ቀንና ሌሊት ቤተ መቅደሱን እየዞሩ ይጠብቁ ነበር።”

የሳንሄድሪን ሸንጎ እነዚህን ፖሊሶች ማዘዝ ይችል ነበር። ሮማውያን መሣሪያ እንዲታጠቅ የሚፈቅዱለት የአይሁዳውያን ቡድን ይህ ብቻ ነበር።

ዮአኪም ዬርምያስ የተባሉ ምሁር እንዲህ ብለዋል፦ “ኢየሱስ በተያዘበት ወቅት ለሰዎቹ በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ያልያዙት ለምን እንደሆነ የጠየቃቸው (ማቴ. 26:55) ሊይዙት የመጡት ሰዎች የቤተ መቅደሱ ፖሊሶች ስለሆኑ መሆን አለበት።” እኚህ ጸሐፊ ከተወሰነ ጊዜ በፊት ኢየሱስን ለመያዝ የተላኩት ሰዎችም የቤተ መቅደስ ፖሊሶች እንደሆኑ ያምናሉ። (ዮሐ. 7:32, 45, 46) ከጊዜ በኋላም ፖሊሶቹና የቤተ መቅደሱ ሹም የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ ይዘው እንዲመጡ ተልከው ነበር፤ ሐዋርያው ጳውሎስንም ከቤተ መቅደሱ ጎትተው ያወጡት እነሱ ሳይሆኑ አይቀሩም።—ሥራ 4:1-3፤ 5:17-27፤ 21:27-30