በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ—ኑሮን በዘዴ

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ—ኑሮን በዘዴ

ዓለም ላይ እንሰማቸው የነበሩ ችግሮች አሁን የአንተንም ቤት እያንኳኩ እንደሆነ ይሰማሃል? አንተ በምትኖርበት አካባቢ ከታች የተጠቀሱት ነገሮች የተለመዱ ሆነዋል?

  • ጦርነት

  • ወረርሽኝ

  • የተፈጥሮ አደጋዎች

  • ድህነት

  • ዘረኝነት

  • ወንጀል

አንድ አሳዛኝ ነገር ሲከሰት ብዙ ሰዎች በጣም ይደነግጣሉ፤ እንዲሁም ተስፋ ያጣሉ። አንዳንዶች ደግሞ የደነዘዙ ያህል ስሜት አልባ ይሆናሉ። ሆኖም አሳዛኝ ነገር በሚከሰትበት ወቅት፣ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ድንጋጤም ሆነ መደንዘዝ ችግሩን ቢያባብሰው እንጂ መፍትሔ አይሆንም።

አንድ ዓይነት ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት ቤተሰብህን፣ ጤናህን፣ መተዳደሪያህን እንዲሁም ደስታህን ለመጠበቅ ቶሎ እርምጃ መውሰድ አለብህ።

ታዲያ በዓለም ላይ የሚከሰቱት ችግሮች በአንተ ላይ የሚፈጥሩትን ጫና ለመቀነስ ምን ማድረግ ትችላለህ?