ንቁ! ቁጥር 2 2019 | ልጆች ሊማሯቸው የሚገቡ ስድስት ትምህርቶች
ልጆች ሊማሯቸው የሚገቡ ስድስት ትምህርቶች
ልጃችሁ ካደገ በኋላ በየትኛው ባሕርይው ተለይቶ እንዲታወቅ ትፈልጋላችሁ?
ራሱን የሚገዛ
ትሑት
ችግሮችን መቋቋም የሚችል
ኃላፊነት የሚሰማው
በሳል
ሐቀኛ
ልጆች እነዚህን ባሕርያት በራሳቸው ሊያዳብሯቸው አይችሉም። የእናንተ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
ይህ መጽሔት ልጆቻችሁን ልታስተምሯቸው የሚገቡ ስድስት አስፈላጊ ትምህርቶችን ያብራራል። ልጆች እነዚህን ትምህርቶች መማራቸው አዋቂ ሲሆኑ ለሚጠብቃቸው ሕይወት ያዘጋጃቸዋል።
ራስን መግዛት
ራስን መግዛት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህን ባሕርይ ማዳበር የሚቻለውስ እንዴት ነው?
ትሕትና
ልጆች ትሕትናን መማራቸው አሁንም ሆነ ወደፊት ይጠቅማቸዋል።
ችግሮችን የመቋቋም ችሎታ
ችግሮችን የመቋቋም ችሎታ ያዳበሩ ልጆች በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መወጣት ቀላል ይሆንላቸዋል።
ኃላፊነት የሚሰማው መሆን
አንድ ሰው ኃላፊነት የሚሰማው መሆንን የሚማረው ልጅ እያለ ነው ወይስ አዋቂ ከሆነ በኋላ?
የአዋቂዎች መመሪያ አስፈላጊነት
ልጆች በሕይወታቸው ውስጥ አስተማማኝ መመሪያ ያስፈልጋቸዋል፤ ለመሆኑ ይህን መመሪያ ማግኘት የሚችሉት ከየት ነው?
የሥነ ምግባር እሴቶች አስፈላጊነት
ልጆቻችሁን በጥሩ የሥነ ምግባር እሴቶች ኮትኩታችሁ ማሳደጋችሁ ለወደፊት ሕይወታቸው ጠንካራ መሠረት ይጥልላቸዋል።
ለወላጆች ተጨማሪ እርዳታ
ወላጆችም ጥሩ ሕይወት ለመምራት አስተማማኝ መመሪያ ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት jw.orgን ተመልከት።