‘የአምላክን ስም በተመለከተ የነበረኝን ጥርጣሬ አስወግዶልኛል’
‘የአምላክን ስም በተመለከተ የነበረኝን ጥርጣሬ አስወግዶልኛል’
ይህን የተናገረው በሳን ዲዬጎ፣ ካሊፎርኒያ የሚኖር የስፓንኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ሰው ነው። ይህ ሰው በዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በላከው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ሲል ገልጿል:- “እኔ የድርጅታችሁ አባል ባልሆንም እንኳ ጽሑፎቻችሁን ማንበብ ያስደስተኛል። ይህን ደብዳቤ የጻፍኩላችሁ አድናቆቴን ለመግለጽ ነው። ከሦስት ቀናት በፊት አንድ ብሮሹር ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ተጥሎ አየሁ። ብሮሹሩ በውኃ ርሶ የነበረ ቢሆንም አነሳሁት። የብሮሹሩ ርዕስ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም የሚል ነው። እንዲደርቅ ካደረግኩ በኋላ በደንብ አነበብኩት።
“እንደዚህ ብሮሹር የማረከኝ ጽሑፍ የለም። በጣም ልዩ የሆነ ብሮሹር ነው። የአምላክን ስም በተመለከተ የነበረኝን ጥርጣሬ ሁሉ አስወግዶልኛል። ይህ ብሮሹር ምንም እንኳ የተጎሳቆለ ቢሆንም ሃይማኖተኛ የሆኑ ጓደኞቼን ስለ አምላክ ስም ለማስተማር እየተጠቀምኩበት ነው። ‘የአምላክ ስም ማነው?’ ብዬ እጠይቃቸዋለሁ። ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት ስለሚያቅታቸው ብሮሹሩን አውጥቼ አሳያቸዋለሁ። እባካችሁ በስፓንኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የዚህን ብሮሹር ሦስት ቅጂዎች ላኩልኝ።”
እርስዎም ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም የተባለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።