ቤተሰብ የሚወያይበት
ቤተሰብ የሚወያይበት
ትክክለኛ ውሳኔ ነበር?
ማርቆስ 12:41-44ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።
1. የመዋጮ ዕቃዎቹ የሚገኙት የት ነበር?
ፍንጭ፦ ማርቆስ 12:35ን እና 13:1ን አንብብ።
․․․․․
2. መበለቲቱ የሰጠችው ገንዘብ በጣም ትንሽ ቢሆንም ኢየሱስ ያደነቃት ለምንድን ነው?
ፍንጭ፦ ማርቆስ 12:28-30ን አንብብ።
․․․․․
3. መበለቲቱ “መተዳደሪያዋን በጠቅላላ” ብትሰጥም እንኳ ችግር ላይ እንዳልወደቀች እርግጠኛ መሆን የምትችለው ለምንድን ነው?
ፍንጭ፦ ማቴዎስ 6:25, 31-33ን አንብብ።
․․․․․
ለውይይት፦
ይህች መበለት ያደረገችው ውሳኔ ትክክል ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? በለጋስነት የመስጠት ልማድ ብታዳብር ምን ጥቅም ታገኛለህ?
ፍንጭ፦ ሉቃስ 6:38ን እና የሐዋርያት ሥራ 20:35ን አንብብ።
ስለ ሐዋርያው ዮሐንስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?
4. የሃይማኖት መሪዎቹ ዮሐንስን የተማረና አንደበተ ርቱዕ ሰው እንደሆነ አድርገው ተመልክተውታል?
ፍንጭ፦ የሐዋርያት ሥራ 4:13ን አንብብ።
․․․․․
5. ዮሐንስ ምን ልዩ መብት ተሰጥቶት ነበር?
ፍንጭ፦ ራእይ 1:1-3ን አንብብ።
ለውይይት፦
ዮሐንስ ስንት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን ጽፏል? ዮሐንስን መምሰል የምትችለው እንዴት ነው?
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
ከዚህ እትም
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።
ገጽ 9 የበለጠ ደስታ የሚያስገኘው ምን ማድረግ ነው? የሐዋርያት ሥራ 20:․․․
ገጽ 9 የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሚታወቁት በምንድን ነው? ዮሐንስ 13:․․․
ገጽ 21 የአምላክ ሰላም ምን ያደርጋል? ፊልጵስዩስ 4:․․․
ገጽ 22 ይሖዋ ለእነማን ቅርብ ነው? መዝሙር 34:․․․
● መልሶቹ በገጽ 21 ላይ ይገኛሉ
በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. በቤተ መቅደሱ ውስጥ።
2. መበለቲቱ የቻለችውን ሁሉ ለአምላክ ስለሰጠች።
3. አምላክ፣ የእሱን ፈቃድ ካስቀደምን እንደሚንከባከበን ቃል ስለገባ።
4. በፍጹም። ከዚህ ይልቅ ዮሐንስን ያልተማረና ተራ ሰው እንደሆነ አድርገው ቆጥረውታል።
5. የራእይን መጽሐፍ ጨምሮ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን በመንፈስ መሪነት የመጻፍ መብት።