በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በታሪክ ሲታወስ የሚኖር የእውቀት ጥማት

በታሪክ ሲታወስ የሚኖር የእውቀት ጥማት

በታሪክ ሲታወስ የሚኖር የእውቀት ጥማት

● ሰዎች በምን ቢያስታውሱህ ደስ ይልሃል? ሌሎች ስለ አንተ ሲያስቡ ወደ አእምሯቸው የሚመጣው ምን ይሆን? ብዙዎች ለትውልድ ትተውት የሚያልፉት ቅርስ ስለሚያሳስባቸው በሳይንስ፣ በፖለቲካ፣ በስፖርትና በኪነ ጥበብ ታዋቂ ለመሆን ይጥራሉ። ይሁንና ሰዎች በተለይ የሚያስታውሱህ ባነሳሃቸው ጥያቄዎች ቢሆን ምን ይሰማሃል?

ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በማዕከላዊ አሜሪካ ይኖር የነበረ አንድ ሰው አመራማሪ የሆኑ ብዙ ጥያቄዎችን ጠይቆ ነበር። ይህ ሰው ኒካራኦ የተባለ የአንድ ጎሣ አለቃ ሲሆን “ኒካራጉዋ” የሚለው መጠሪያ የመጣው ከእሱ ስም ሳይሆን አይቀርም። የዚህ ሰው ስም የራሱን ጎሣ፣ የኖረበትን አገርና በዚያ ያለውን ትልቅ ሐይቅ ያመለክታል።

የኒካራኦ ጎሣ በፓሲፊክ ውቅያኖስና ኒካራጉዋ በተባለው ግዙፍ ሐይቅ መካከል በምትገኝ መሬት ላይ ይኖር ነበር። ኮሎምበስ የአሜሪካን አህጉራት ካገኘ ብዙም ሳይቆይ ስፔናውያን ይህን አካባቢ ለማሰስ ተነሱ። ካፒቴን ሂል ጎንዛሌዝ ዳቪላ፣ ሠራዊቱን እየመራ አሁን ኮስታ ሪካ ከሚባለው አገር በስተሰሜን በመጓዝ በ1523 ዓ.ም. ወደ ኒካራኦ ምድር ገባ።

አሳሾቹ ከዚያ በፊት በማያውቁት አካባቢ ሲጓዙ ሊሰማቸው የሚችለውን ስጋት አስበው። እነዚህ ሰዎች፣ ኒካራኦ ከተባለው የጎሣው አለቃ ጋር ሲገናኙ ምንኛ ተደስተው ይሆን! ሕዝቡ ስፔናውያኑን ተቀብሎ ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን ሰጣቸው፤ ኒክራጓውያን አሁንም ድረስ በልግስናቸው ይታወቃሉ።

ኒካራኦ ሲያሳስቡት ለኖሩት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ፈልጎ ነበር። ስፔናውያኑን ማግኘቱም ሌሎች ጥያቄዎች እንዲፈጠሩበት አደረገ። ኒካራኦ ለካፒቴን ጎንዛሌዝ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዳቀረበ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘግበዋል፦

ሰዎችንና እንስሳትን በሙሉ ስላጠፋ ታላቅ ጎርፍ ሰምተህ ታውቃለህ? አምላክ ምድርን እንደገና በጎርፍ ያጥለቀልቃት ይሆን? ስንሞት ምን እንሆናለን? ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የሚንቀሳቀሱት እንዴት ነው? በሰማይ ላይ የተንጠለጠሉት እንዴት ነው? ከእኛ ምን ያህል ይርቃሉ? ብርሃን መስጠታቸውን የሚያቆሙትስ መቼ ነው? ነፋስ የሚመጣው ከየት ነው? ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ ብርሃንና ጨለማ እንዲፈራረቁ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? በዓመቱ ውስጥ የቀኑ ርዝማኔ የሚለዋወጠው ለምንድን ነው?

በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ኒካራኦ በዙሪያው ስላለው ዓለም የማወቅ ጉጉት ነበረው። ያነሳቸው ጥያቄዎች ስለሚያምናቸው ነገሮች የሚጠቁሙት ብዙ ነገር አለ። እሱ ለማወቅ የፈለጋቸውና ያሳሰቡት ነገሮች በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ከሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ጋር እንደሚመሳሰሉ ካነሳቸው ነጥቦች መረዳት ይቻላል። እንዲሁም ኒካራኦና ሕዝቡ ስለ አንድ ታላቅ የጎርፍ መጥለቅለቅ ማወቃቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ዘገባ ያስታውሰናል።​—ዘፍጥረት 7:17-19

ኒካራኦ የሚኖርበት ማኅበረሰብ በመናፍስታዊ ድርጊቶች የተጠላለፈ ከመሆኑም ሌላ አምልኮው ሰዎችን መሥዋዕት ማድረግን ያካትት የነበረ ቢሆንም ኒካራኦ የሕዝቡ ምግባርና አኗኗር ያሳስበው ነበር። ያነሳቸው ጥያቄዎች ሕሊና ስለሚያከናውነው ተግባር ምሥክርነት ይሰጣሉ። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ሕሊና ሲጽፍ “ሕሊናቸው ከእነሱ ጋር ሆኖ በሚመሠክርበት ጊዜ ሐሳባቸው በውስጣቸው እየተሟገተ አንዴ ይከሳቸዋል ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥፋተኛ አይደላችሁም ይላቸዋል” ብሏል።​—ሮም 2:14, 15

ስፔናውያን መጀመሪያ ሲመጡ ከኒካራኦ ጋር እንደተገናኙ በሚታሰብበት ቦታ ላይ በዛሬው ጊዜ ለኒካራኦ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞለታል። ስለ ሕይወትና በዙሪያው ስላለው ዓለም በጥልቅ እንዲያስብ ያነሳሳው የእውቀት ጥማት ለእኛም ጥሩ ምሳሌ ይሆናል።​—ሮም 1:20

[በገጽ 21 ላይ የሚገኝ ካርታ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ኒካራጉዋ

ደቡብ አሜሪካ

አትላንቲክ ውቅያኖስ