ንቁ! ግንቦት 2015 | ቤት የሌላቸውና ድሆች ምን ተስፋ አላቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ ቤት የሌላቸውንና ድሆችን በአሁኑ ጊዜ መርዳት ስለሚቻልበት መንገድ ከመናገሩም በተጨማሪ ወደፊት የቤት እጦትና ድህነት ከነጭራሹ እንደሚወገዱ ይናገራል።

ከዓለም አካባቢ

የዜናው ትኩረት—እስያ

እስያ ውስጥ ያሉ አገሮች ሕዝባቸውን በማስተማርና በመጠበቅ ረገድ ምን ተፈታታኝ ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ ሊረዳቸው ይችላል?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ቤት የሌላቸውና ድሆች ምን ተስፋ አላቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ምክር በኢኮኖሚ ረገድ የተረጋጋ ሕይወት እንድንመራና የአእምሮ ሰላም እንድናገኝ ይረዳናል።

ለቤተሰብ

ልጆች ታዛዥ እንዲሆኑ ማሠልጠን

እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ከልጆቻችሁ ጋር ትጨቃጨቃላችሁ? እንዲህ የመሰለውን ጭቅጭቅ ለማስቀረት ወላጆችን የሚረዱ አምስት ነጥቦች።

“አምላክ ፈውስ ማግኘት እንድንችል ረድቶናል”

በ2004 በቤስላን የሚገኘው ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት በተሰነዘረበት ወቅት የታገቱት ሦስት ሰዎች ሁኔታው ያስከተለባቸውን የስሜት ቀውስ መቋቋም የቻሉት እንዴት እንደሆነ ገልጸዋል።

የታሪክ መስኮት

አል ክዋሪዝሚ

በስምንተኛው መቶ ዘመን የኖረው ዓረብ “እስከ ዛሬ ከተፈለሰፉት የስሌት ዘዴዎች ሁሉ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት” ዘዴ አስተዋውቋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ዓመፅ

አምላክ ለዓመፅ ምን አመለካከት አለው? ዓመፀኞች ሊለወጡ ይችላሉ?

ንድፍ አውጪ አለው?

ብርሃን አመንጪው የሃዋይ ቦብቴይል ስኩዊድ

እንስሳው የራሱን ብርሃን የሚፈጥረው ለማየት ወይ ለመታየት አይደለም።

በተጨማሪም . . .

በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል?

አንተው ራስህ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

እባክህ እና አመሰግናለሁ

ካሌብ እነዚህን ቃላት መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ተማረ።