መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መጋቢት 2013

ይህ እትም ሁሉም ክርስቲያኖች ለሕይወት የሚያደርጉትን ሩጫ እንዳያቋርጡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያሳስባቸዋል። በተጨማሪም ልባችንንም ሆነ አምላካችንን ይሖዋን ለማወቅ የሚያስችል ማስተዋል ይሰጠናል።

ይሖዋን የሚወዱ ‘ዕንቅፋት የለባቸውም’

የይሖዋን ሕግ የሚወዱ እንቅፋት የለባቸውም ሊባል የሚችለው ከምን አንጻር ነው? ለሕይወት የምናደርገውን ሩጫ እንዳናቋርጥ ምን ሊረዳን እንደሚችል ተመልከት።

ይሖዋን “የሚያውቅ ልብ” አለህ?

ነቢዩ ኤርምያስ የተናገራቸው ቃላት ጤናማ የሆነ ምሳሌያዊ ልብ ማግኘትና እንዲህ ያለ ልብ ይዘህ መኖር እንድትችል ይረዱሃል።

“አምላክን አውቃችኋል”—ከዚህ በኋላስ?

እምነትህንም ሆነ ለይሖዋ አምላክ ምን ያህል ያደርክ እንደሆንክ ዘወትር መመርመርህ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ተመልከት።

ተጽናኑ—ሌሎችንም አጽናኑ

ሁሉም ሰው የጤና ችግር ያጋጥመዋል፤ እንዲያውም አንዳንዶች በጠና ይታመማሉ። እንዲህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም የምንችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ መጠጊያችን ነው

የምንኖረው ክፉ በሆነ ዓለም ውስጥ ቢሆንም ይሖዋ ሕዝቡን እንደሚጠብቅ እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

የይሖዋን ታላቅ ስም አክብሩ

የይሖዋን ስም የመጠቀም መብትህን እንዴት ትመለከተዋለህ? የአምላክን ስም ማወቅና በስሙ መሄድ ሲባል ምን ማለት ነው?

በእርግጥ ጆሴፈስ ጽፎታል?

ቴስቲሞንየም ፍላቭያነም የሚባለውን ምንባብ የጻፈው አይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ ፍላቪየስ ጆሴፈስ ነው?

ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ!

አንድ ሰው እውነትን አይቀበልም ብላችሁ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጡ። ከጊዜ በኋላ እውነትን የተቀበሉ ሰዎችን ተሞክሮ እንድታነብ እንጋብዝሃለን። እነዚህ ሰዎች እውነትን ሊቀበሉ የቻሉት ለምን እንደሆነ ተመልከት።