መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መጋቢት 2014
በዚህ እትም ውስጥ፣ የራስን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግን መንፈስና ስለ ራሳችን አዎንታዊ አመለካከት ይዘን መቀጠል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይብራራል። በዕድሜ የገፉ የእምነት ባልንጀሮቻችንን እና ዘመዶቻችንን መንከባከብ የምንችለው እንዴት ነው?
የማያምኑ ዘመዶቻችንን ልብ መንካት
ኢየሱስ ዘመዶቹን ከያዘበት መንገድ ምን ትምህርት እናገኛለን? ከእኛ የተለየ እምነት ላላቸው ወይም ጨርሶ እምነት ለሌላቸው ዘመዶቻችንን ስለ እምነታችን መናገር የምንችለው እንዴት ነው?
የራስን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግን መንፈስ ይዘን መቀጠል የምንችለው እንዴት ነው?
የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈሳችን ቀስ በቀስ እንዲዳከም የሚያደርግ አንድ ጠላት አለን። ይህ ጠላት ማን እንደሆነ እንዲሁም እሱን ለመቋቋም መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀም የምንችለው እንዴት እንደሆነ በዚህ ርዕስ ላይ ይብራራል።
አዎንታዊ አመለካከት ይዘን ይዘን መቀጠል የምንችለው እንዴት ነው?
ብዙዎች አሉታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው አስተዋጽኦ የሚያደርጉት ነገሮች ምንድን ናቸው? ይህ ርዕስ ስለ ራሳችን አዎንታዊ አመለካከት ይዘን ለመቀጠል መጽሐፍ ቅዱስ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
የቤተሰብ አምልኮ—ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ማድረግ ትችላላችሁ?
በተለያዩ አገሮች ያሉ ወንድሞች የቤተሰብ አምልኳቸውን እንዴት እንደሚያከናውኑ በማንበብ እናንተም ምን ማድረግ እንደምትችሉ ጠቃሚ ሐሳቦችን ማግኘት ትችላላችሁ።
በመካከላችሁ ያሉትን አረጋውያን አክብሯቸው
አምላክ ለአረጋውያን ያለው አመለካከት እንድትመረምር እንጋብዝሃለን። ራሳቸውን ችለው የሚኖሩ ልጆች በዕድሜ የገፉ ወላጆቻቸውን በመንከባከብ ረገድ ምን ኃላፊነት አለባቸው? ጉባኤዎች በዕድሜ የገፉ ክርስቲያኖችን እንደሚያከብሩ ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?
አረጋውያንን መንከባከብ
በዕድሜ የገፉ ወላጆችም ሆኑ ልጆች ‘የጭንቀት ጊዜ’ ሳይመጣ አስቀድመው አንዳንድ ዝግጅቶችንና ውሳኔዎችን ማድረግ ይችላሉ። አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም የሚችሉት እንዴት ነው?
ቃላችሁ—“አዎ ሆኖ እያለ አይደለም” ነው?
ክርስቲያኖች ቃላቸውን መጠበቅ እንዲሁም ቃላቸው “አዎ ሆኖ እያለ አይደለም” እንዳይሆን ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። አንድን ፕሮግራም ለመሰረዝ የሚያስገድድ ሁኔታ ቢያጋጥመንስ? ሐዋርያው ጳውሎስ የተወውን ምሳሌ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።