በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

አምላክ ምን ዓይነት ነው?

አምላክ በዓይን የማይታይ መንፈሳዊ አካል ነው። ሰማያትን፣ ምድርንና ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ የፈጠረው እሱ ነው። አምላክን ማንም አልፈጠረውም፤ መጀመሪያም የለውም። (መዝሙር 90:2) አምላክ ሰዎች ወደ እሱ እንዲቀርቡና ስለ እሱ እውነቱን እንዲያውቁ ይፈልጋል።—የሐዋርያት ሥራ 17:24-27ን አንብብ።

አምላክ የግል ስም ያለው መንፈሳዊ አካል ነው። በፍጥረት ሥራዎቹ ላይ በማሰላሰል አንዳንድ ባሕርያቱን ማስተዋል እንችላለን። (ሮም 1:20) ይሁንና ስለ አምላክ በሚገባ ለማወቅ ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ግሩም ባሕርያት እንድናውቅ ያስችለናል።—መዝሙር 103:7-10ን አንብብ።

አምላክ ስለ ፍትሕ መጓደል ምን ይሰማዋል?

ፈጣሪያችን ይሖዋ የፍትሕ መጓደልን ይጠላል። ሰዎችንም ቢሆን የፈጠራቸው በራሱ አምሳል ነው። (ዘዳግም 25:16) ብዙዎቻችን የፍትሕ መጓደልን የምንጠላው ለዚህ ነው። በአካባቢያችን እየተፈጸመ ላለው የፍትሕ መጓደል ተጠያቂው አምላክ አይደለም። አምላክ ለሰው ልጆች የመምረጥ ነፃነት ሰጥቷቸዋል። የሚያሳዝነው ግን ብዙ ሰዎች የመምረጥ ነፃነታቸውን አላግባብ የሚጠቀሙበት ሲሆን ፍትሕ የጎደለው ድርጊትም ይፈጽማሉ። ይሖዋ ይህን ሲመለከት ልቡ እጅግ ያዝናል።—ዘፍጥረት 6:5, 6ን እና ዘዳግም 32:4, 5ን አንብብ።

ይሖዋ ፍትሕን ይወዳል፤ ስለሆነም የፍትሕ መጓደልን ለዘላለም ታግሦ አይኖርም። (መዝሙር 37:28, 29) መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ በቅርቡ ማንኛውንም ዓይነት የፍትሕ መጓደል እንደሚያስወግድ ይገልጻል።—2 ጴጥሮስ 3:7-9, 13ን አንብብ

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ በቅርቡ ፍትሕ እንደሚያሰፍን ይገልጻል