መዝሙር 79
ጸንተው እንዲቆሙ አስተምሯቸው
-
1. ደስ ይላል፣ ማስተማር ቅኖችን
ማየት እድገታቸውን፤
እውነትም ሲሆን የራሳቸው፣
ይሖዋ ሲመራቸው።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ስማን ’ባክህ
በ’የሱስ ስም ስንለምንህ፤
ጥበቃህ አይለያቸው።
ምኞታችን በርትተው ማየት ነው፣ ጸንተው።
-
2. ስንጸልይ ነበር በየ’ለቱ፤
ፈተናን እንዲወጡ።
አስተማርን፣ ረዳን ጊዜ ሰጥተን፤
እነሱም በረቱልን።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ስማን ’ባክህ
በ’የሱስ ስም ስንለምንህ፤
ጥበቃህ አይለያቸው።
ምኞታችን በርትተው ማየት ነው፣ ጸንተው።
-
3. ባምላክ ላይ ይሁን ትምክ’ታቸው፤
ድፍረት እንዲኖራቸው።
ታዛዦች ከሆኑ፣ ከጸኑ፤
ለሕይወት ይበቃሉ።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ስማን ’ባክህ
በ’የሱስ ስም ስንለምንህ፤
ጥበቃህ አይለያቸው።
ምኞታችን በርትተው ማየት ነው፣ ጸንተው።