በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Thai Liang Lim/E+ via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ማኅበራዊ ሚዲያ ልጃችሁን እየጎዳው ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ለወላጆች የሚሰጠው ምክር

ማኅበራዊ ሚዲያ ልጃችሁን እየጎዳው ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ለወላጆች የሚሰጠው ምክር

 “በወጣቶች ላይ እየታየ ያለው የአእምሮ ጤና ቀውስ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ለዚህ ዋነኛው መንስኤ ደግሞ ማኅበራዊ ሚዲያ እንደሆነ ተስተውሏል።”—የአሜሪካ የማኅበረሰብ ጤና ባለሥልጣን የሆኑት ዶክተር ቪቬክ ሙርቲ፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ሰኔ 17, 2024

 ወላጆች፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ከሚያስከትለው አደጋ ልጆቻቸውን መጠበቅ የሚችሉት እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ምክሮች ይዟል።

ወላጆች ምን ማድረግ ይችላሉ?

 እስቲ እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮች ተመልከት።

 “ብልህ ግን አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል።”—ምሳሌ 14:15

 ማኅበራዊ ሚዲያ ካሉት አደጋዎች አንጻር ልጃችሁን እንዳይጠቀም ብትከለክሉት ስህተት እንደሆነ አይሰማችሁ። ልጃችሁ ማኅበራዊ ሚዲያ እንዲጠቀም ከመፍቀዳችሁ በፊት የፈቀዳችሁለትን የጊዜ ገደብ ማክበር፣ ጤናማ ወዳጅነት መመሥረትና ተገቢ ካልሆነ ነገር መራቅ የሚችልበት የብስለት ደረጃ ላይ መድረሱን አረጋግጡ።

 “ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት።”—ኤፌሶን 5:16

 ልጃችሁ ማኅበራዊ ሚዲያ እንዲጠቀም ከፈቀዳችሁ ስለ አጠቃቀሙ ደንቦች አውጡ፤ እንዲሁም እነዚህ ደንቦች ለደህንነቱ እንደሚጠቅሙት አስረዱት። በልጃችሁ ጠባይ ላይ ለውጥ ካለ በንቃት ተከታተሉ፤ ይህ በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀሙ ላይ ተጨማሪ ገደብ መጣል እንዳለባችሁ የሚጠቁም ሊሆን ይችላል።

ግንዛቤያችሁን አስፉ

 መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የምንኖረው “ለመቋቋም [በሚያስቸግር] በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን” ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) መጽሐፍ ቅዱስ የዘመኑን አስከፊነት ከመናገር ባለፈ ሁኔታውን ለመቋቋም የሚረዱ ዘመን የማይሽራቸው ምክሮች ይዞልናል። በወጣቶች የአእምሮ ጤና ላይ ያተኮረው ይህ ርዕስ ለወላጆችና ለልጆች ታስበው የተዘጋጁ ከ20 በላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎችን ይዘረዝራል።