በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Marek M. Berezowski/Anadolu Agency via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

የዩክሬን ጦርነት ሁለተኛ ዓመቱን ያዘ—መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ተስፋ አለ?

የዩክሬን ጦርነት ሁለተኛ ዓመቱን ያዘ—መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ተስፋ አለ?

 አሳዛኙ የዩክሬን ጦርነት ከጀመረ ዓርብ፣ የካቲት 24, 2023 አንድ ዓመት ይሞላዋል። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት 300,000 ገደማ የዩክሬንና የሩሲያ ወታደሮች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል፤ 30,000 ገደማ የሚሆኑ ንጹሐንም በጦርነቱ እንደሞቱ ይታመናል። ይሁንና ቁጥሩ ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል ይጠበቃል።

 የሚያሳዝነው ደግሞ ጦርነቱ በቅርቡ መቋጫ የሚያገኝ አይመስልም።

  •   “የሩሲያ ሠራዊት ዩክሬን ከገባ ዓመት ሊሞላው ነው፤ ሆኖም ግጭቱ እልባት ያገኛል እንድንል የሚያደርግ ምንም ጭላንጭል አይታይም። ሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ ድል የሚቀናቸው አይመስልም፤ በድርድር ጠረጴዛ ለመፍታት የሚደርገው ጥረትም ተስፋ አስቆራጭ ይመስላል።”—ብሔራዊ የሕዝብ ሬዲዮ፣ የካቲት 19, 2023

 ይህም ሆነ በዓለም ዙሪያ የተከሰቱ ሌሎች ግጭቶች በንጹሐን ላይ ከፍተኛ ሰቆቃና መከራ እያደረሱ ነው፤ ታዲያ ይህ ጦርነት ብዙዎችን ቢያስጨንቅ ምን ይገርማል? ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ የሚሰጥ ሐሳብ ይዞ ይሆን? ስለ ጦርነት የማንሰማበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ጦርነቶችን ሁሉ የሚያስቀር ጦርነት

 የሰውን ልጅ የሚያጠፋ ሳይሆን የሚታደግ አንድ ጦርነት እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ ጦርነት አርማጌዶን ተብሎ ይጠራል፤ ‘ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን የሚካሄድ ጦርነት’ ተብሎም ተገልጿል። (ራእይ 16:14, 16) በዚህ ጦርነት አማካኝነት አምላክ ለብዙ አውዳሚ ጦርነቶች መንስኤ የሆነውን የሰዎች አስተዳደር ያጠፋል። አርማጌዶን ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍነው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ የሚከተሉትን ርዕሶች አንብብ፦