በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 7, 2022
ምያንማር

አዲስ ዓለም ትርጉም በካረን (ስጋው) ቋንቋ ወጣ

አዲስ ዓለም ትርጉም በካረን (ስጋው) ቋንቋ ወጣ

መጋቢት 27, 2022 የምያንማር ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ማትስ ካስሆልም አዲስ ዓለም ትርጉም በካረን (ስጋው) ቋንቋ በዲጂታል ፎርማት መውጣቱን አበሰረ። አስቀድሞ የተቀረጸውን ፕሮግራም 620 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ተከታትለዋል። የታተመውን መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያዝያ 2022 ጀምሮ ማግኘት ይቻላል።

በምያንማር የይሖዋ ምሥክሮች ታሪክ የጀመረው በ1914 የመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እዚያ በደረሱበት ጊዜ ነው። ከ1940 በኋላ የካረን (ስጋው) ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው የመጀመሪያው አስፋፊ በምያንማር ተጠመቀ።

አዲስ ዓለም ትርጉም በዚህ ቋንቋ መዘጋጀቱ በጣም ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም በካረን (ስጋው) የተዘጋጁት ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ለመረዳት አስቸጋሪ የሆኑ ወይም የተሳሳተ መልእክት የሚያስተላልፉ ጥንታዊ ቃላትን ይዘዋል። ለምሳሌ አንድ የካረን (ስጋው) መጽሐፍ ቅዱስ፣ መዝሙር 72:16⁠ን “በምድር ላይ አንድ እፍኝ እህል ይኖራል” ብሎ ተርጉሞታል። አዲስ ዓለም ትርጉም ግን ጥቅሱን “በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል” በማለት በትክክል ተርጉሞታል።

ይህ መጽሐፍ ቅዱስ መውጣቱ የካረን (ስጋው) ቋንቋ ተናጋሪ ለሆኑ አስፋፊዎች ትልቅ መንፈሳዊ በረከት ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ በመንፈሳዊ ጠንካራ ሆነው እንዲቀጥሉ እንዲረዳቸው እንጸልያለን።—1 ጴጥሮስ 5:10