በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ሬይማንና ባለቤቱ ቫለሪያ ጥቅምት 9, 2020 ፍርድ ቤት ውስጥ ሆነው

ጥቅምት 9, 2020
ሩሲያ

ሩሲያ ፍርድ ቤት በአንድ ወጣት ባልና ሚስት ላይ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላለፈ፤ በገደብ እስራት እንዲቀጡም ወስኗል

ሩሲያ ፍርድ ቤት በአንድ ወጣት ባልና ሚስት ላይ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላለፈ፤ በገደብ እስራት እንዲቀጡም ወስኗል

በኮስትሮማ የሚገኘው የስቭርድሎቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ጥቅምት 9, 2020 ወንድም ሰርጌ ሬይማን እና ባለቤቱ እህት ቫለሪያ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ውሳኔ አስተላለፈ። ወንድም ሰርጌ ለስምንት ዓመት እህት ቫለሪያ ደግሞ ለሰባት ዓመት የገደብ እስር ተፈርዶባቸዋል። ይህ ፍርድ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2017 ከጣለው እገዳ በኋላ በወንድሞቻችን ላይ የተፈረደው ረጅሙ የገደብ እስር ነው። ወንድም ሰርጌና ባለቤቱ አሁን እስር ቤት ገብተው አይታሰሩም ማለት ነው።