በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ከባለቤቱ ከናታሊያ ጋር

ጥቅምት 14, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወንድም ስፒሪን ላይ የተላለፈው ፍርድ እንዲጸና ወሰነ

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወንድም ስፒሪን ላይ የተላለፈው ፍርድ እንዲጸና ወሰነ

ጥቅምት 14, 2020 የኢቫኖቮ ክልል ፍርድ ቤት በወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ላይ የተላለፈው የመጀመሪያ ፍርድ እንዲጸና ወሰነ። ወንድም ዬቭጌኒ ሐምሌ 2020 ጥፋተኛ ነው ተብሎ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበት ነበር። አቃቤ ሕግ የወንድም ስፒሪን ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ ያቀረበውን ጥያቄ የክልሉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል። አቃቤ ሕግ ወንድም ስፒሪን ለሰባት ዓመት እንዲታሰር መጀመሪያ ላይ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ አሁን በተላለፈው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ሊጠይቅ ይችላል።