በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ከፍተኛ ቁጥር አስመዘገቡ

የይሖዋ ምሥክሮች ከፍተኛ ቁጥር አስመዘገቡ

በ1987 የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል አባል የሆነው ላይማን ስዊንግል ቫሌንሲያ፣ ቬኔዙዌላ ውስጥ ፕላዛ ሞኑሜንታል በሚባል ከኮርማዎች ጋር የሚደረግ ትግል በሚታይበት ስፍራ ለተሰበሰቡ 63,580 ሰዎች ንግግር አቅርቦ ነበር። ብዙዎች የእሱን ንግግር ለመስማት ሌሊቱን ሙሉ በአውቶቡስ ተጉዘዋል። ወንድም ስዊንግል ለተሰበሰበው ሕዝብ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “የእናንተ ቅርንጫፍ ቢሮ ትንሽ የሚባል መሆኑ ቀርቷል። አሁን ቅርንጫፍ ቢሯችሁ መካከለኛ ደረጃ ላይ ነው። በዚህ አያያዛችሁ በቅርቡ 100,000 አስፋፊዎች ካሏቸው አገራት መካከል ትሆናላችሁ።”

በ1987 ቬኔዙዌላ ውስጥ የነበሩት አስፋፊዎች ማለትም የአምላክን መንግሥት ምሥራች የሚያውጁ የይሖዋ ምሥክሮች ከ38,000 በላይ ነበሩ። በዚያን ጊዜ ከ100,000 በላይ አስፋፊዎች የነበሯቸው አገሮች ስምንት ብቻ ነበሩ።

የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ አስገራሚ እድገት አድርገዋል። ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ስለ ይሖዋ መንግሥት የሚሰብኩ ሰዎች ብዛት በጥቂት ሺዎች የሚቆጠር ነበር። ሆኖም ይህ ሁኔታ ተቀየረ። የ1943 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ከአንዳንድ አካባቢዎች ጋር ያለን ግንኙነት በመቋረጡ የ1942 አጠቃላይ ሪፖርት የተሟላ ባይሆንም እንኳ እንደተባረክን የሚያሳይ ነው . . . ምክንያቱም ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ በሥራው [ማለትም ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ] እየተካፈሉ ያሉት አስፋፊዎች ከ106,000 በላይ ናቸው።” በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በነበረው ቀውጢ ጊዜም እንኳ ብዙ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጥሩ ምላሽ ሰጥተዋል። በ1950 በዩናይትድ ስቴትስ ብቻ እንኳ ከ100,000 በላይ አስፋፊዎች ነበሩ።

ከ100,000 በላይ አስፋፊዎችን ያስመዘገበችው ሁለተኛዋ አገር ናይጄሪያ ስትሆን ይህ ሪፖርት የተመዘገበው በ1974 ነበር።

በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ብራዚል እና ጀርመን ከ100,000 በላይ አስፋፊዎችን አስመዝግበዋል። በአራቱም አህጉራት የታየው እንዲህ ያለው እድገት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በዓለም ዙሪያ ተቀባይነት እንዳገኘ የሚያሳይ ማስረጃ ነው።

ለምሥራቹ ጥሩ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ብዛት በዓለም ዙሪያ እየጨመረ ሄዷል። ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኘው ከሚከተለው ትንቢት ጋር ይስማማል፦“ጥቂት የሆነው ሺህ፣ ትንሽ የሆነውም ኃያል ብሔር ይሆናል። እኔ ይሖዋ፣ ይህን በራሱ ጊዜ አፋጥነዋለሁ።”—ኢሳይያስ 60:22

የ2014 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት እንደሚያሳየው ከ100,000 በላይ የይሖዋ ምሥክሮች ያሏቸው አገሮች ብዛት 24 ደርሷል። ከእነዚህ አገሮች መካከል አንዷ ቬኔዙዌላ ስትሆን እዚህ ቁጥር ላይ የደረሰችው በ2007 ነው። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ 115,416 የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች እንዲሁም 8,201,545 አስፋፊዎች ይገኛሉ።

ከ100,000 በላይ አስፋፊዎች ያሏቸው አገሮች

አህጉር

አገር

አስፋፊ

አፍሪካ

አንጎላ

108,607

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ

216,024

ጋና

125,443

ናይጄሪያ

362,462

ዛምቢያ

178,481

እስያ

ጃፓን

215,703

ኮሪያ ሪፑብሊክ

100,641

ፊሊፒንስ

196,249

አውሮፓ

ብሪታንያ

138,515

ፈረንሳይ

127,961

ጀርመን

166,262

ጣሊያን

251,650

ፖላንድ

123,177

ሩሲያ

171,268

ስፔን

112,493

ዩክሬን

150,906

ሰሜን አሜሪካ

ካናዳ

116,312

ሜክሲኮ

829,523

ዩናይትድ ስቴትስ

1,243,387

ደቡብ አሜሪካ

አርጀንቲና

150,171

ብራዚል

794,766

ኮሎምቢያ

166,049

ፔሩ

123,251

ቬኔዙዌላ

140,226